ፓራዳይም  ዩኒቨርስቲ

ፓራዳይም ዩኒቨርስቲ ለዘመናዊ የከፍተኛ ትምህርት አቅርቦት

ስልክ:+251-911-616802 ከጠዋቱ 2 ሰዓት - ምሽቱ 1 ሰዓት

ዲግሪዎን በ100% የኦንላየን ሞዴል ለመከታተል በመወሰንዎ በርካታ ጊዜ፣ ገንዘብና ጉልበት አትርፈዋል፡፡

በኦንላይን ትምህርት የሚያገኙት ዲግሪ በነባር የትምህርት አሰጣጥ ከሚገኝ ዲግሪ እኩል ጥራትና ተቀባነት አለው፡፡ ለዚህም ነው የኦንላየን ዲግሪ ፕሮግራሞቻችን ከHERQA ሙሉ ዕውቅና የተሰጣቸው፡

የትምህርት መተግበሪያችንን ስልክዎ ላይ በመጫን በየትኛውም ቦታ ጥናትዎን መከወን ይችላሉ፡፡

እያንዳንዱ ኮርስ በአግባቡ የተዘጋጀ የቪዲዮ ሌክቸር፣ ፓወር ፖይንት ስላይድ፣ የመማሪያ መጽሐፍ. የመልመጃ ጥያቄዎች ከነመልሶቻነቸው እንዲሁም ሳምንታዊና የማጠቃለያ ፈተናዎችን ያካተተ በመሆኑ በግልዎ ፍጥነትዎ ልክ ቀንም ሆነ ሌሊት በተመቸዎ ሰዓት ለመማር ያስችላል፡፡

በኮርስዎ ሂደት የሚያጋጥምዎን አካዳሚያዊ ጥያቄዎችን ለመመለስ ፕሮፌሰሮቻችን ቢያንስ በሴሚስተር ሶስት ጊዜ በግል ወይም ከክፍል ጓደኞችዎ ጋር በቡድን በቀጥታ የቪዲዮ ፎረም መረሃ-ግብር ቀርጸው ይጠብቅዎታል፡፡

ዘመናዊው የትምህርት ማሳለጫ መተግበሪያችን በርካታ አካዳሚያዊ ተግባራትን ለማከናወን የሚያስችል በመሆኑ ሳምንታዊ ቴስቶችን፣ የቤት ስራዎችን፣ እንዲሁም የማጠቃለያ ፈተናዎችን 100 ቤትዎ ኦንላየን ለመውሰድ ያስችሎታል፡፡

ይህም ማለት ፈተና ለመፈተን ረጅም ርቀት መጓዝ አይጠበቅብዎትም፡፡

በዲጂታል ቤተመጻህፍታችን ውስጥ ከ 40,000 በላይ የመጻህፍት ስብስብ ያለን ሲሆን ተመራማሪዎች ምቹ የሆኑ ከ100 በላይ የጥናትና ምርምር ጆርናል ቤተመጻህፍቶች ከመካነ ድራችን ጋር ተያይዘዋል፡፡ በየትኛውም የዓለማችን ክፍል ሆነው ለአጠቃቀም ቀላልና አስተማማኝ አገልግሎት ያገኛሉ፡፡

እጅግ ዘመናዊ የሆነው የትምህርት አስተዳደር መተግበሪያችንን በመጠቀም በዩኒቨርስቲው የመረጃ ቋት ተመዝግቦ የሚገኘውን የእርስዎን የግል ማህደር፣ የክፍያ አፈጻጸምዎን፣ የወሰዱትናና በቀጣይ የሚወሲዷቸውን ኮርሶች እንዲሁም ውጤትዎን ዘና ብለው መመልከት ወይም በወረቀት ማተም ይችላሉ፡፡ 

የትምህርት ክፍያዎን ለመፈጸም ጥሬ ገንዘብ ወደ ዩኒቨርስቲው ቢሮ ስለመምጣት ፈጽሞ አያስቡ፡፡ በርካታ የክፍያ መፈጸሚያ አማራጮችን ስላዘጋጀን በኦንላየን፣ በእጅ ስልክዎ ወይም በአካባቢዎ በሚገኝ ባንክ በአካውንታችን በማስገባት መፈጸም ይችላሉ፡፡

የዋናው ካምፓሳችን አድራሻ

  • የሥራ ሰዓት

ከሰኞ – አርብ

8:00 AM – 5:00 PM

ቅዳሜ እና እሁድ

10:00 AM – 5:00 PM

  • አድራሻችን

አየር ጤና ዕድገት በኅብረት ህንጻ

1ኛ ፎቅ፣ 

ፖስታ: 506-1033

አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ

ስልክ

+251-911-616802

ኢሜይል:

info@paradigm.edu.et

info@paradigm.university

መካነ-ድር:

www.paradigm.edu.et

www.paradigm.university

  • ካርታ